እርስዎ ወይም ለእርስዎ ቅርብ የሆነ ሰው ማስፈራሪያዎች፣ ጥቃቶች ወይም ጭቆናዎች እያጋጠሙዎ ነው? ሊያገኙት የሚችሉት እርዳታ አለ፡፡ ወደ ድጋፍ መስመሮቻችን መደወል ወይም ከእኛ ጋር መወያየት ይችላሉ፡፡ ድጋፍ፣ ምክር እና መረጃ ያገኛሉ፡፡
• ብዙ ቋንቋዎችን እንናገራለን፡፡
• ሙሉ የሆነ ምስጢራዊነትን እንጠብቃለን፡፡
• ስምዎን አለመግለጽ ይችላሉ፡፡
• ጥሪዎች በስልክ ሂሳብ ላይ የማይታዩ እና ነጻ ናቸው፡፡
በሚፈልጉት ነገር ላይ በመመስረት ወደ እኛ ሲደዉሉ ምን እንደሚሆን ይወስናሉ። ማግኘት የሚችሉት ነገር፤
• ያጋጠሙዎትን ነገር ለማስሄድ ይረዳል፣
• ስለ ህጎች እና ስለ እርስዎ መብቶች መረጃ፣
• ወደ የት እንደሚዞር መረጃ እና ምክር
• ጠበቃ፣ ማህበራዊ አገልግሎቶች ወይም ፖሊስን ለማግኘት እገዛ ማግኘት
የፈለጉትን ያህል ጊዜ ሊደውሉልን ይችላሉ፡፡ እርስዎ ሊነግሩን የሚፈልጉትን እርስዎ ይወስናሉ፣ እና እኛ ደግሞ እርስዎ የጠየቁንን ነገር ብቻ እናደርጋለን፡፡
ጠበኝነት እርስዎ ሳያውቁት በግንኙነት ውስጥ ሊያድግ ይችላል፣ እና እየተገበሩት ያለዉ ነገር እንደ ሁከት መቆጠሩን አለማወቅ የተለመደ ነው፡፡ ሁከት በአንድ ወይም ከዛ በላይ በሆኑ ሰዎች ሊፈጸም ይችላል፡፡ ለምሳሌ አመጽ የሚከተለዉ ሊሆን ይችላል፤
• አካላዊ
• ወሲባዊ
• ሥነ-ልቦናዊ / ስሜታዊ
• ቁሳቁሳዊ ወይም ገንዘብ ነክ የሆነ
በስልክ ቁጥር፦ 020-81 82 83
ከሰኞ – አርብ፦ 09:00-16:00
ኢሜይል፦ stodjouren@somaya.se
Somaya ለተጎዱ አዋቂዎችና ለልጆቻቸው ደህንነቱ የተጠበቀ ማረፊያ ይሰጣል፡፡ ከመላው ስዊድን የመጡ ሴቶችን፣ ወንዶችን እና LGBTQI ሰዎችን እንቀበላለን፡፡ አብዛኛው ምደባ የሚከናወነው በማኅበራዊ አገልግሎት በኩል ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በስዌድሽ ፍልሰት ቦርድ በኩል ነው።
ደህንነቱ በተጠበቀ ቤታችን ውስጥ በሚቆዩበት ጊዜ የመጀመሪያ ጊዜው አመፅ እና ማስፈራሪያ ከተጠቀመበት ሰው / ሰዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ስለማቋረጥ ነው፡፡ ተግባራዊ እና ስሜታዊ ድጋፍ ያገኛሉ ፡፡ የፖሊስ ሪፖርት ማቅረብ ከፈለጉ ምክር ለማግኘት ከጠበቃ ጋር እንዲገናኙ እናግዝዎታለን፡፡ እንዲሁም ከባለስልጣናት፣ ከጤና አጠባበቅ እና ትምህርት ቤቶች ጋር ለመገናኘት እንደግፍዎታለን፡፡
በማረፊያችን ውስጥ እያንዳንዱ ሰው ሊቆለፍ የሚችል የራሱ ክፍል ያገኛል ፡፡ እንደ ወጥ ቤት፣ ሳሎን እና መታጠቢያ ቤት ያሉ በአንድ ላይ ያሉ ቦታዎች ይጋራሉ፡፡ የራስዎን ምግብ ለመግዛት እና ምግብ ለማብሰል ሃላፊነት አለብዎት።
ደህንነቱ በተጠበቀ ቤታችን ውስጥ በሚቆዩበት ጊዜ፣ በተለያዩ የማበረታቻ እንቅስቃሴዎች ውስጥ መሳተፍ ይችላሉ እናም የራስዎትን ኑሮ ለመኖር ድጋፍ ያገኛሉ፡፡
የ Somaya ለአቅመ ሄዋን የደረሱ እና ያልደረሱ ሴቶች መጠለያ ለትርፍ ያልተቋቋመ ማህበር ነው፡፡ ለአመፅ የተጋለጡ እና / ወይም በክብር ላይ በተመሰረተ ጭቆና አብረው የሚኖሩ የውጭ ሴቶችን፣ ወንዶችን እና የ LGBTQI ሰዎችን እንደግፋለን ፡፡ ከ 20 ዓመት በላይ ልምድ አለን እና የብዙ ቋንቋዎች ተናጋሪዎች ነን፡፡ እኛ የድጋፍ መስመር፣ የንግግር፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ቤት እና የእንቅስቃሴ ማዕከል አለን፡፡